ከአንተ ዘንድ የመጡ አይሁድ ወደ እኛ ወደ ኢየሩሳሌም እንደመጡ በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ዓመፀኛይቱንና ክፉይቱን ከተማ በመስራት፥ ቅጥሮቿንም በማደስ፥ መሠረትዋንም በመጠገን ላይ ናቸው።
ዮሐንስ 18:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጲላጦስ መልሶ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ወገኖችህና የካህናት አለቆች ለእኔ አሳልፈው ሰጡህ፤ ምን አድርገሃል?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጲላጦስም መልሶ፣ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ወደ እኔ የላኩህ የራስህ ወገኖችና የካህናት አለቆች ናቸው፤ ለመሆኑ ምን አድርገህ ነው?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጲላጦስም “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? አንተን ለእኔ አሳልፈው የሰጡህ ወገኖችህና የካህናት አለቆች ናቸው፤ ምንድን ነው ያደረግኸው?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጲላጦስም መልሶ፥ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ለእኔ አሳልፈው የሰጡህ ወገኖችህና ሊቃነ ካህናት አይደሉምን? Aረ ምን አድርገሃል?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጲላጦስ መልሶ፦ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ወገኖችህና የካህናት አለቆች ለእኔ አሳልፈው ሰጡህ፤ ምን አድርገሃል?” አለው። |
ከአንተ ዘንድ የመጡ አይሁድ ወደ እኛ ወደ ኢየሩሳሌም እንደመጡ በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ዓመፀኛይቱንና ክፉይቱን ከተማ በመስራት፥ ቅጥሮቿንም በማደስ፥ መሠረትዋንም በመጠገን ላይ ናቸው።
ኢየሱስንም ከቀያፋ ወደ ገዢው ግቢ ወሰዱት፤ ማለዳም ነበረ፤ እነርሱም እንዳይረክሱ፥ ይልቁንም የፋሲካን በግ እንዲበሉ በማለት ወደ ገዢው ግቢ አልገቡም።
ኢየሱስም መልሶ “መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግሥቴ ከዚህ ዓለም ብትሆን ኖሮ፥ ወደ አይሁድ እንዳልሰጥ ሎሌዎቼ ይዋጉልኝ ነበር፤ ነገር ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለችም” አለው።
ኢየሱስም መልሶ “ከላይ ባይሰጥህ ኖሮ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን ባልኖረህ ነበር፤ ስለዚህ ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ሰው ኀጢአቱ የባሰ ነው” አለው።
የካህናት አለቆችና ሎሌዎችም ባዩት ጊዜ “ስቀለው! ስቀለው!” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም “እኔስ አንዲት በደል እንኳን አላገኘሁበትምና እናንተ ወስዳችሁ ስቀሉት” አላቸው።
የአብርሀምና የይስሐቅ የያዕቆብም አምላክ፥ የአባቶቻችን አምላክ፥ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና ሊፈታው ቆርጦ ሳለ በጲላጦስ ፊት የካዳችሁትን ብላቴናውን ኢየሱስን አከበረው።