ዮሐንስ 17:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከዓለም ወስጥ ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ፤ ለእኔም ሰጠሃቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእነዚህ ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገልጬላቸዋለሁ። የአንተ ነበሩ ለእኔ ሰጠኸኝ፤ እነርሱም ቃልህን ጠብቀዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዓለም ውስጥ መርጠህ ለሰጠኸኝ ሰዎች የአንተን ማንነት ገለጥኩላቸው፤ እነርሱ የአንተ ነበሩ፤ አንተ እነርሱን ለእኔ ሰጠኸኝ፤ እነርሱም ቃልህን ጠብቀዋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከዓለም ለይተህ ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁ፤ ያንተ ነበሩ፤ እነርሱንም ለእኔ ሰጥተኸኛል፤ ቃልህንም ጠበቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ ለእኔም ሰጠሃቸው፤ |
ከእነርሱ ጋር በዓለም ሳለሁ የሰጠኸኝን እኔ በስምህ እጠብቃቸው ነበር፤ ጠበቅኋቸውም፤ የመጽሐፉም ቃል እንዲፈጸም ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም።
አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር በፊት ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ፥ የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ።
አይሁድ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን አወቅን። አብርሃም እንኳን ሞተ፤ ነቢያትም እንዲሁ፤ አንተ ግን ‘ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘለዓለም ሞትን አይቀምስም፤’ ትላለህ።
እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝቡን አልጣላቸውም። ወይስ ኤልያስ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እስራኤል እንዴት እንደተከራከረ መጽሐፍ ምን እንደሚል አታውቁምን?
በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት እንዲሰጥ ብርሃን በልባችን ውስጥ ያበራ፥ “በጨለማ ብርሃን ይብራ፤” ያለው እግዚአብሔር ነው።
የክርስቶስ ቃል በሙላት በእናንተ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩም፤ በመዝሙርና በውዳሴ በመንፈሳዊም ዝማሬ በልባችሁ በማመስገን ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤
የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ፥ እውነት የሆነውን እንድናውቅ ማስተዋልን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነት በሆነው በእርሱ እንኖራለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።
“የት እንደምትኖር አውቃለሁ፥ የሰይጣን ዙፋን ባለበት ነው፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፤ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ በእኔ ያለህን እምነት አልካድህም።
“ሥራህን አውቃለሁ፤ እነሆ በአንተ ፊት የተከፈተ በር ሰጥቼአለሁ፤ ማንም ሊዘጋውም አይችልም፤ ኃይልህ ምንም ትንሽ ቢሆን ቃሌን ጠብቀሃልና፤ ስሜንም አልካድህምና።