ዮሐንስ 17:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃልህ እውነት ነው፤ በእውነትህ ቀድሳቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው። |
እኛም ሁላችን፥ በመጋረጃ በማይሸፈን ፊት፥ የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን፥ የእርሱን መልክ እንድንመስል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን፥ ይህም መንፈስ ከሚሆን ጌታ የመጣ ነው።
በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! እኛ ግን ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ልናመሰግን ይገባናል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከመጀመሪያው አንሥቶ በመንፈስ በመቀደስና በእውነት በማመን እንድትድኑ መርጦአችኋልና፤