ዮሐንስ 15:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳሩ ግን የላከኝን አያውቁምና ይህን ሁሉ በስሜ ምክንያት ያደርጉባችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የላከኝን ስለማያውቁ፣ በስሜ ምክንያት ይህን ያደርጉባችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የላከኝን ስለማያውቁ በእኔ ምክንያት ይህን ሁሉ ያደርጉባችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ስለ ስሜ ይህን ሁሉ ያደርጉባችኋል፤ የላከኝን አያውቁትምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳሩ ግን የላከኝን አያውቁምና ይህን ሁሉ ሰለ ስሜ ያደርጉባችኋል። |
እናንት በቃሉ ፊት የምትርዱ፥ የጌታን ቃል ስሙ፦ የጠሉአችሁ የናንተው ሕዝብ፥ ስለ ስሜም ያባረሩአችሁ፦ “ደስታችሁን እንድናይ ጌታ ይክበር” ብለዋል፤ ነገር ግን ያፍራሉ።
ከዚህም ሁሉ በፊት እጃቸውን በላያችሁ ጭነው ይይዟችኋል፤ ያሳድዱአችኋ፤ ስለ ስሜም ወደ ምኵራብና ወደ ወኅኒ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ወደ ነገሥታትና ወደ ገዥዎችም ይወስዱአችኋል፤
ስለዚህም “አባትህ ወዴት ነው?” አሉት። ኢየሱስ መልሶ “እኔንም ሆነ አባቴንም አታውቁም፤ እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ደግሞ ባወቃችሁ ነበር፤” አላቸው።
ነገር ግን አላወቃችሁትም፤ እኔ ግን አውቀዋለሁ። አላውቀውም ብል ኖሮ እንደ እናንተ ሐሰተኛ በሆንሁ ነበር፤ ዳሩ ግን አውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ።
የምታመልኩትን እየተመለከትሁ ሳልፍ ‘ለማይታወቅ አምላክ’ የሚል ጽሕፈት ያለበትን መሠዊያ ደግሞ አግኝቼአለሁና። እንግዲህ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን እኔ እነግራችኋለሁ።
ነገር ግን በሕዝቡ ዘንድ አብዝቶ እንዳይስፋፋ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ለማንም ሰው በዚህ ስም እንዳይናገሩ እየዛትን እንዘዛቸው፤” ብለው እርስ በርሳቸው ተማከሩ።
የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፤ እንዲሁም ነን። ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛንም አያውቀንም።