La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 12:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከአይሁድም ብዙ ሰዎች በዚያ እንደ ነበረ አውቀው መጡ፤ የመጡትም በኢየሱስ ምክንያት ብቻ ሳይሆን ከሙታን ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ ብዙ አይሁድ ኢየሱስ በዚያ መኖሩን ዐውቀው መጡ፤ የመጡትም ኢየሱስን ብለው ብቻ ሳይሆን፣ እርሱ ከሙታን ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያን ጊዜ ከአይሁድ ብዙዎች ኢየሱስ በቢታንያ መሆኑን ዐውቀው መጡ፤ የመጡትም ስለ ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ ከሞት ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከአ​ይ​ሁ​ድም ብዙ ሰዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በዚያ እን​ዳለ በዐ​ወቁ ጊዜ ወደ እርሱ መጡ፤ የመ​ጡ​ትም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ለማ​የት ብቻ አል​ነ​በ​ረም፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣ​ዉን አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ያዩ ዘንድ ነበር እንጂ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከአይሁድም ብዙ ሕዝብ በዚያ እንደ ነበረ አውቀው መጡ፥ ከሙታንም ያስነሣውን አልዓዛርን ደግሞ እንዲያዩ ነበረ እንጂ ስለ ኢየሱስ ብቻ አይደለም።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 12:9
8 Referencias Cruzadas  

“ታዲያ ዳዊት ራሱ ጌታ፥ ካለው፤ እንዴት ተመልሶ ልጁ ይሆናል?”። ብዙ ሕዝብም በደስታ ይሰማው ነበር።


ከፋሲካም በፊት በስድስተኛው ቀን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ።


የካህናት አለቆችም አልዓዛርን ሊገድሉት ተማከሩ፤


በማግሥቱ ወደ በዓሉ መጥቶ የነበረው ብዙ ሕዝብ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመጣ በሰማ ጊዜ፥


አልዓዛርንም ከመቃብር ጠርቶ ከሙታን ሲያስነሣው ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝብ ይመሰክሩለት ነበር።


የተፈወሰውንም ሰው ከእነርሱ ጋር ቆሞ ሲያዩ የሚመልሱትን አጡ።