La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 10:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሌሎችም “ይህ ጋኔን ያለበት ሰው ቃል አይደለም፤ ጋኔን የዐይነ ሥውሮችን ዐይን ሊከፍት ይችላልን?” አሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሌሎች ግን፣ “ይህ ጋኔን ያደረበት ሰው ንግግር አይደለም፤ ጋኔን የዐይነ ስውርን ዐይን መክፈት ይችላልን?” አሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሌሎች “ይህ ንግግር ጋኔን ካለበት ሰው አንደበት የሚወጣ አይደለም፤ ጋኔን የዕውርን ዐይን ማብራት ይችላልን?” አሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሌሎ​ችም ይህ ነገር ጋኔን ከያ​ዘው ሰው የሚ​ገኝ አይ​ደ​ለም፤ ጋኔን የዕ​ዉ​ሮ​ችን ዐይን ማብ​ራት ይች​ላ​ልን?” አሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሌሎችም፦ “ይህ ጋኔን ያለበት ሰው ቃል አይደለም፤ ጋኔን የዕውሮችን ዓይኖች ሊከፍት ይችላልን?” አሉ።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 10:21
11 Referencias Cruzadas  

ጌታ የዕውሮችን ዐይን ያበራል፥ ጌታ የወደቁትን ያነሣል፥ ጌታ ጻድቃንን ይወድዳል፥


ጆሮን የተከለው አይሰማምን? ዓይንን የሠራው አያይምን?


ጌታም እንዲህ አለው፦ “የሰውን አፍ የፈጠረ ማን ነው? ዲዳ ወይም ደንቆሮ ወይም የሚያይ ወይም ዕውር ያደረገ ማን ነው? እኔ ጌታ አይደለሁምን?


በሕዝቤና በሕዝብህ መካከል ልዩነት አደርጋለሁ፤ ይህም ምልክት ነገ ይሆናል።’”


የሚሰማ ጆሮንና የሚያይ ዓይንን፥ ሁለቱን ጌታ ፈጠራቸው።


ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶች ይራመዳሉ፤ ለምጻሞችም ይነጻሉ፤ ደንቆሮዎች ይሰማሉ፤ ሙታን ይነሣሉ፤ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤


ዝናው በመላዋ ሶርያ ሁሉ ተሰማ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይ ተይዘው የታመሙትን ሁሉ፥ አጋንንት ያደሩባቸውን፥ በጨረቃ የሚነሣባቸውንና ሽባዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።


በኢየሩሳሌምም የመቅደስ መታደስ በዓል ሆነ፤ ወቅቱም የብርድ ጊዜ ነበር።


ይህንንም ብሎ ወደ መሬት እንትፍ አለ፤ በምራቁም ጭቃ አድርጎ በጭቃው የዐይነ ሥውሩን ዐይኖች ቀባና