La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 6:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በውኑ የሜዳ አህያ ሣር እያለው ይጮኻልን? ወይስ በሬ ገለባ እያለው ይጮኻልን?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሜዳ አህያ ሣር እያለው፣ በሬስ ድርቆሽ እያለው፣ ይጮኻልን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በውኑ የሜዳ አህያ ለምለም ሣር ካገኘ በሬም ድርቆሽ ካገኘ ይጮኻልን?

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በውኑ የሜዳ አህያ ሣር እያ​ለው በከ​ንቱ ይጮ​ኻ​ልን? የሚ​በ​ላ​ውን ፈልጎ አይ​ደ​ለ​ምን? ወይስ በሬ በበ​ረት ውስጥ ገለባ ሳለው ይጮ​ኻ​ልን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በውኑ የሜዳ አህያ ሣር ሳለው ይጮኻልን? ወይስ በሬ ገለባ ሳለው ይጮኻልን?

Ver Capítulo



ኢዮብ 6:5
8 Referencias Cruzadas  

በእኛ ዘንድ ገለባና ገፈራ የሚበቃ ያህል አለ፥ ለማደሪያም ደግሞ ስፍራ አለን።”


የሜዳውንስ አህያ ማን ነፃ ለቀቀው? የበረሃውንስ አህያ ከእስራቱ ማን ፈታው?


ተራራውን እንደ መሰማርያው ይቃኘዋል፥ ለምለሙንም ሣር በሙሉ ይፈልጋል።


የማይጣፍጥስ ነገር ያለ ጨው ይበላልን? ወይስ የእንቁላል ውኃ ይጥማልን?


እንጀራን ከምድር ያወጣ ዘንድ ሣርን ለእንስሳ፥ ለምለሙንም ለሰው ልጆች ጥቅም ያበቅላል።


ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች ትምህርት።


የሜዳ አህዮችም በተራቈቱ ኮረብቶች ላይ ቆመዋል፥ እንደ ቀበሮም ወደ ነፋስ አለከለኩ፤ ልምላሜም የለምና ዐይኖቻቸው ጠወለጉ።