ኢዮብ 5:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ችግር ከትቢያ አይመጣም፥ መከራም ከመሬት አይበቅልም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ችግር ከምድር አይፈልቅም፤ መከራም ከመሬት አይበቅልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ችግር ከዐፈር አይነሣም፤ መከራም ከመሬት አይበቅልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ችግር ከምድር አይወጣምና፥ መከራም ከተራሮች አይበቅልምና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ችግር ከትቢያ አይመጣም፥ መከራም ከመሬት አይበቅልም፥ |
የማይረባውን ቃላት ተናገሩ፤ በሐሰት መሐላ ቃል ኪዳን አደረጉ፤ ስለዚህ መርዛም አረም በእርሻ ትልሞች ላይ እንደሚበቅል መቅሠፍት በቀለባቸው።
በመከርህ ማንም ሰው ሳይዘራው የበቀለውን አትሰብስብ፥ ያልተገረዘውን የወይንህን ተክል ፍሬ አታከማች፤ ለምድሪቱ የዕረፍት ሰንበት ዓመት ይሁን።
ከዚያም ወዴት እንደሚሄድ ተመልከቱ፤ ወደ ገዛ አገሩ ወደ ቤትሼሜሽ አቅጣጫ የሚሄድ ከሆነ፥ ይህን ታላቅ መከራ ያመጣብን እርሱ ነው። ወደዚያ ካልሄደ ግን፥ መከራው በአጋጣሚ የደረሰብን እንጂ የእርሱ እጅ እንዳልመታን እናውቃለን።”