ኢዮብ 42:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ኢዮብ መቶ አርባ ዓመት ኖረ፥ ልጆቹንና የልጅ ልጆቹንም እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ኢዮብ አንድ መቶ አርባ ዓመት ኖረ፤ ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኢዮብ መቶ አርባ ዓመት ኖረ፤ የልጅ ልጆቹንም እስከ አራት ትውልድ ድረስ ለማየት በቃ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮብም ከደዌው ከዳነ በኋላ መቶ ሰባ ዓመት ኖረ፥ ኢዮብም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሁለት መቶ አርባ ነው። ልጆቹንና የልጅ ልጆቹንም እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በኋላ ኢዮብ መቶ አርባ ዓመት ኖረ፥ ልጆቹንና የልጅ ልጆቹንም እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ። |