ኢዮብ 41:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀላዩን እንደ ድስት ያፈላዋል፥ ባሕሩንም እንደ ሽቱ ምንቸት ያደርገዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሥጋው ንብርብር እርስ በርስ የተጣበቀ፣ በላዩ የጸናና ከቦታው የማይናጋ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥጋው ድርብርብ ሆኖ እርስ በርሱ የተጣበቀ ስለ ሆነ ሰውነቱ እንደ ብረት የጠነከረ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሲኦልም ጥልቀት እንደ ምርኮ ነው። ቀላዩንም እንደ መመላለሻ መንገድ ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀላዩን እንደ ድስት ያፈላዋል፥ ባሕሩንም እንደ ሽቱ ምንቸት ያደርገዋል። |
የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አውርድ፥ እንዲህም በለው፦ በሕዝቦች መካከል አንበሳ መሰልህ፥ እንደ ባሕር አውሬ ነበርህ፤ በወንዞችህም ገንፍለህ ወጥተሃል፥ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም አሳድፈሃል።