እነሆ፥ እኔ የሽብር ወሬ የሚያሰማ መንፈስ እልክበታለሁ፤ ስለዚህም ወደ አገሩ ተመልሶ እንዲሄድና እዚያም በገዛ ምድሩ በሰይፍ ተመትቶ እንዲሞት አደርጋለሁ።’”
ኢዮብ 4:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፥ በቁጣውም መንፈስ ያልቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፤ በቍጣውም ወላፈን ይደመሰሳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፤ በቊጣውም ማዕበል ይደመሰሳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይጠፋሉ፥ በቍጣውም መንፈስ ያልቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፥ በቍጣውም መንፈስ ያልቃሉ። |
እነሆ፥ እኔ የሽብር ወሬ የሚያሰማ መንፈስ እልክበታለሁ፤ ስለዚህም ወደ አገሩ ተመልሶ እንዲሄድና እዚያም በገዛ ምድሩ በሰይፍ ተመትቶ እንዲሞት አደርጋለሁ።’”
እነሆም፥ ብርቱ ነፋስ ከምድረበዳ መጥቶ የቤቱን አራቱን ማዕዘን መታው፥ በብላቴኖቹም ላይ ወደቀ፥ ሞቱም፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ።”
ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤ በአፉ በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የጌታም እስትንፋስ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።