ኢዮብ 39:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከተማ ውካታ ይስቃል፥ የነጂውን ጩኸት አይሰማም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በከተማ ውካታ ይሥቃል፤ የነጂውንም ጩኸት አይሰማም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁካታ ከበዛባቸው ከተሞች ርቀው ይኖራሉ፤ ከኋላ እየነዳ የሚጮኽባቸውን አይቀበሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በከተማው ሕዝብ ውካታ ይዘብታል፤ የሚያስፈራውንም ጩኸት አይሰማም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በከተማ ውካታ ይዘብታል፥ የነጂውን ጩኸት አይሰማም። |
ጌታም እንዲህ ይለኛልና፦ አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ ሲያገሣ፥ ብዙ እረኞች ቢከማቹበት ከቃላቸው እንደማይፈራ ከድምፃቸውም እንደማይዋረድ፥ እንደዚሁም የሠራዊት ጌታ በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ለመዋጋት ይወርዳል።
“ስለምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም?” ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።