ኢዮብ 39:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነውጥና በቁጣ መሬትን ይውጣል፥ የመለከትም ድምፅ ቢሰማ አይቆምም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በወኔ መሬቱን እየጐደፈረ ወደ ፊት ይሸመጥጣል፤ የመለከት ድምፅ ሲሰማ ያቅበጠብጠዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እምቢልታው ሲነፋ ሲቃ ይዞአቸው በጭካኔና በቊጣ ወደ ጦር ሜዳ ይሸመጥጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቍጣውም መሬትን ያጠፋል፤ የመለከትም ድምፅ እስከሚሰማው አያምንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጭካኔና በቍጣ መሬትን ይውጣል፥ የመለከትም ድምፅ ቢሰማ አይቆምም። |
አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፥ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፤ ነፍሴ ሆይ! የመለከትን ድምፅና የጦርነትን ሁካታ ሰምተሻልና ዝም ማለት አልችልም።
አደመጥሁ ሰማሁም፤ ቅንን ነገር አልተናገሩም፤ አንድም ሰው፦ ‘ምን አድርጌአለሁ?’ ብሎ ከክፋቱ ንስሐ የገባ የለም፤ ወደ ጦርነትም እንደሚሮጥ ፈረስ እያንዳንዱ በየመንገዱ ይሄዳል።