ኢዮብ 39:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሸለቆው ውስጥ በኮቴው ይጐደፍራል፥ በጉልበቱም ደስ ይለዋል፥ ሰይፍ የታጠቁትንም ለመጋፈጥ ይወጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጕልበቱ እየተመካ በብርቱ ይጐደፍራል፤ ጦርነት ሊገጥም ይወጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈረሶቹ ወደ ጦር ሜዳ ተጋልበው ሲሄዱ በጒልበታቸው በመመካት ሶምሶማ ይረግጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኮቴው በሸለቆው ውስጥ ይጐደፍራል፥ በጕልበቱም ወደ ሜዳ ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኮቴው በሸለቆው ውስጥ ይጐደፍራል፥ በጉልበቱም ደስ ይለዋል፥ ሰይፍም የታጠቁትን ለመገናኘት ይወጣል። |
አደመጥሁ ሰማሁም፤ ቅንን ነገር አልተናገሩም፤ አንድም ሰው፦ ‘ምን አድርጌአለሁ?’ ብሎ ከክፋቱ ንስሐ የገባ የለም፤ ወደ ጦርነትም እንደሚሮጥ ፈረስ እያንዳንዱ በየመንገዱ ይሄዳል።