ኢዮብ 39:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእርሷ ያልሆኑ ይመስል በልጆችዋ ትጨክናለች፥ ድካምዋ ከንቱም ሊሆን ቢችልም አትፈራም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእርሷ እንዳልሆኑ ሁሉ በልጆቿ ትጨክናለች፤ ድካሟም በከንቱ ቢቀር ደንታ የላትም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጫጩቶችዋ የእርስዋ እንዳልሆኑ አድርጋ ትጨክንባቸዋለች፤ ድካምዋ ሁሉ በከንቱ ቢቀር ደንታ የላትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእርስዋ እንዳልሆኑ በልጆችዋ ላይ ትጨክናለች፤ ያለ ፍርሀትም በከንቱ ትሠራለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእርስዋ እንዳልሆኑ በልጆችዋ ትጨክናለች፥ በከንቱም ብትሠራ አትፈራም፥ |
ሬስ። አቤቱ፥ እይ፥ በማን ላይ እንደዚህ እንዳደረግህ ተመልከት። በውኑ ሴቶች ፍሬያቸውን፥ ያቀማጠሉአቸውን ሕፃናት፥ ይበላሉን? በውኑ ካህኑና ነቢዩ በጌታ መቅደስ ውስጥ ይገደላሉን?