ኢዮብ 39:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጐሽ እንዲተልምልህ ልታጠምደው ትችላለህን? ወይስ ከአንተ በኋላ በእርሻ ላይ ይጐለጉላልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲያርስልህ ልትጠምደው ትችላለህ? ወይስ እየተከተለህ ዕርሻህን ይጐለጕልልሃልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጐሽን ጠምደህ ሞፈር እየጐተተ እንዲያርስ ልታደርገው ትችላለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቀንበር ትጠምደዋለህን? በእርሻህስ ውስጥ ትልም ያርስልሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጐሽ ይተልምልህ ዘንድ ትጠምደዋለህን? ወይስ ከአንተ በኋላ በእርሻ ላይ ይጐለጕላልን? |
በላኪሽ የምትቀመጪ ሆይ፥ ሠረገላውን ከፈረሱ ጋር አያይዢ፤ እርሷ ለጽዮን ሴት ልጆች የኃጢአት መጀመሪያ ነበረች፤ የእስራኤል በደል በአንቺ ዘንድ ተገኝቶአልና።