በይሁዳ ከተማዎችና በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ባሉት ስፍራዎች ሁሉ በየኰረብታው ላይ በነበሩት መሠዊያዎች መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ የይሁዳ ነገሥታት ሾመዋቸው የነበሩትን ካህናት ሁሉ ከሥራ አሰናበተ፤ በዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ፥ ለፀሐይ፥ ለጨረቃ፥ ፀሐይን ለሚዞሩ ዓለማትና ለከዋክብት መሥዋዕት በማቅረብ የሚያገለግሉ ካህናትን ሁሉ ሻረ፤
ኢዮብ 38:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይስ ማዛሮት የሚባሉትን ከዋክብት በጊዜያቸው ታወጣ ዘንድ፥ ወይስ ድብ የሚባለውን ኮከብ ከልጆቹ ጋር ትመራ ዘንድ ትችላለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማዛሮት የተባለውን የከዋክብት ክምችት በወቅቱ ልታወጣ፣ ወይም ድብ የተባለውን ኮከብና ልጆቹን ልትመራ ትችላለህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዋክብትን ሁሉ በየወቅታቸው ማሰማራት ትችላለህን? የድብ ቅርጽ ያላቸውን ከዋክብትስ ከልጆቻቸው ጋር መምራት ትችላለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይስ ማዛሮት የሚባሉትን ከዋክብት በጊዜያቸው ታወጣ ዘንድ፥ ወይስ የምሽቱን ኮከብ ከልጆቹ ጋር ትመራ ዘንድ ትችላለህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይስ ማዛሮት የሚባሉትን ከዋክብት በጊዜያቸው ታወጣ ዘንድ፥ ወይስ ድብ የሚባለውን ኮከብ ከልጆቹ ጋር ትመራ ዘንድ ትችላለህን? |