መብረቅን በእጆቹ ይይዛል፥ ያዘዘውንም እንዲመታ ያደርገዋል፥
እጆቹን በመብረቅ ይሞላቸዋል፤ ዒላማውንም እንዲመታ ያዝዘዋል።
መብረቅን በእጁ ይይዛል፤ ወደተወሰነለትም አቅጣጫ እንዲሄድ ያዘዋል።
በእጁ ብርሃንን ይሰውራል፥ አደጋ የሚጥልባትንም አዘዘ።
እጆቹን በብርሃን ይሰውራል፥ በጠላቱም ላይ ይወጣ ዘንድ ያዝዘዋል፥
የዙፋኑን ፊት ይሸፍናል፥ ደመናውንም ይዘረጋበታል።
የውኃውንም ሙላት በደመና ላይ ይጭናል፥ የብርሃኑንም ደመና ይበታትናል፥
ለተግሣጽ ወይም ለምድሩ ወይም ለምሕረትም ቢሆን፥ ሰው በሚኖርበት ዓለም ላይ ያዘዘውን ሁሉ ያደርግ ዘንድ ፈቃዱ ወደ መራቸው ይዞራሉ።
በውኑ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚያዝዛቸው፥ የደመናውንም ብርሃን እንዴት እንደሚያበራ አውቀሃልን?
መብረቆች ሄደው፦ ‘እነሆ፥ እዚህ አለን’ ይሉህ ዘንድ፥ ልትልካቸው ትችላለህን?
ከምድር ዳርቻ ደመናትን ያወጣል፥ በዝናብ ጊዜ መብረቅን ያደርጋል፥ ነፋሳትንም ከመዛግብቱ ያወጣል።
እሳትና በረዶ አመዳይና ጉም፥ ቃሉን የሚፈጽም ዐውሎ ነፋስም፥
በኪሩቤልም ሠረገላ ላይ ተቀምጦ በረረ፥ በነፋስም ክንፍ አንዣበበ።
ፍላጻውን ላከ በተናቸውም፥ መብረቆችን አበዛ አወካቸውም።
ብዙ ቀንም ፀሐይን ከዋክብትንም ሳናይ ትልቅ ነፋስም ሲበረታብን ጊዜ፥ ወደ ፊት እንድናለን የማለት ተስፋ ሁሉ ተቆረጠ።