ኢዮብ 36:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የደመናውንም መዘርጋት፥ የማደሪያውንም ነጐድጓድ የሚያስተውል ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደመናትን እንዴት እንደሚዘረጋ፣ ከድንኳኑም እንዴት እንደሚያንጐደጕድ ሊረዳ የሚችል ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ደመናውን እንዴት እንደሚዘረጋና በነጐድጓድም ውስጥ ሆኖ እንዴት እንደሚናገር፥ ማን ሊረዳ ይችላል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንድ ሰው የደመናውን መዘርጋት፥ ወይም የማደሪያውን ልክ ቢያውቅ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የደመናውንም መዘርጋት፥ የማደሪያውንም ነጐድጓድ የሚያስተውል ማን ነው? |
የሰማይን ደመና በጥበቡ ሊቈጥር የሚችል ማን ነው? ትቢያ በተበጠበጠ ጊዜ፥ ጓሎቹም በተጣበቁ ጊዜ፥ የሰማይን ደመና ለዝናብ ሊያዘነብል የሚችል ማን ነው?
እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፥ በእርሷም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥
ጌታ ለቁጣ የዘገየ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ በደለኛውንም፦ ንጹሕ ነህ አይልም፤ ጌታ መንገዱ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ነው፥ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።