“እናንተ ጥበበኞች፥ ቃሌን ስሙ፥ እናንተም አዋቂዎች፥ ወደ እኔ አድምጡ።
“እናንተ ጠቢባን፣ ቃሌን ስሙ፤ ዐዋቂዎችም አድምጡኝ።
“እናንተ ጠቢባን የምናገረውን ስሙኝ፤ እናንተም ዐዋቂዎች አድምጡኝ።
“እናንተ ጥበበኞች፥ ቃሌን ስሙ፤ እናንተም ዐዋቂዎች፥ መልካም ነገርን አድምጡ።
እናንተ ጥበበኞች፥ ቃሌን ስሙ፥ እናንተም አዋቂዎች፥ ወደ እኔ አድምጡ።
ኤሊሁም ደግሞ መለሰ፤ እንዲህም አለ፦
ምላስ መብልን እንደሚያጣጥም፥ ጆሮም ቃላትን ይለያልና።
ጠቢብ እነዚህን በመስማት ዐዋቂነትን ይጨምራል፥ አስተዋይም መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል።
ልባሞች እንደ መሆናችሁ እላለሁ፤ የምለውን ነገር እናንተ ፍረዱ።
ወንድሞች ሆይ፤ በአስተሳሰባችሁ ሕፃናት አትሁኑ፤ ለክፉ ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአስተሳሰባችሁ ግን ጐልማሶች ሁኑ።