ይህ ከአንተ ይራቅ፥ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?”
ኢዮብ 34:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ጽድቅን የሚጠላ ሊገዛ ይገባዋልን? ጻድቅና ኃያል የሆነውንስ በደለኛ ታደርገዋለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍትሕን የሚጠላ ሊያስተዳድር ይችላልን? አንተስ ጻድቁንና ኀያል የሆነውን ትኰንናለህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍትሕን የሚጠላ መግዛት ይችላልን? ጻድቁንና ኀያሉን እግዚአብሔር በደለኛ ታደርገዋለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግፍን የሚጠላ፥ ክፉዎችንም የሚያጠፋ፥ ለዘለዓለም ጻድቅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ጽድቅን የሚጠላ ይሠለጥናልን? ጻድቅና ኃያል የሆነውስ በደለኛ ታደርገዋለህን? |
ይህ ከአንተ ይራቅ፥ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?”