የምትናገረው ቢኖርህ መልስልኝ፥ ትክክል መሆንህን እወድዳለሁና ተናገር።
የምትለው ካለህ፣ መልስ ስጠኝ፤ ትክክለኛነትህንም ማወቅ እፈልጋለሁና ተናገር፤
የምትለው ነገር ካለህ መልስልኝ፤ እኔ አንተን ነጻ ለማውጣት ስለምፈልግ ተናገር።
ነገር ቢኖርህ ተናገር፤ ትጸድቅ ዘንድ እወድዳለሁና ተናገር።
ነገር ቢኖርህ መልስልኝ፥ ትጸድቅ ዘንድ እወድዳለሁና ተናገር።
“እነሆ፥ ሐሳባችሁን፥ የመከራችሁብኝንም ክፉ ምክር አውቄዋለሁ።
እናንተን ማጽደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፥ እስክሞት ድረስ ንጹሕነቴን ከእኔ አላርቅም።
ኢዮብ ሆይ፥ አድምጥ፥ እኔንም ስማ፥ ዝም በል፥ እኔም እናገራለሁ።
አለበለዚያም እኔን ስማ፥ ዝም በል፥ እኔም ጥበብን አስተምርሃለሁ።”
ይቻልህ እንደሆነ መልስልኝ፥ የምትለውን አዘጋጅተህ በፊቴ ቁም።