ንጉሡም ሮብዓም፦ “ለዚህ ሕዝብ እንድመልስለት የምትመክሩኝ ነገር ምንድነው?” ብሎ አባቱ ሰሎሞን በሕይወት ሳለ በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ሽማግሌዎች ጋር ተማከረ።
ኢዮብ 32:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደዚህም አልሁ፦ ‘ዕድሜ ይናገር፥ ረጅም ዕድሜም ጥበብን ያስታውቅ።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ዕድሜ ይናገራል፤ ረዥም ዘመን ጥበብን ያስተምራል’ ብዬ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ሽማግሌዎች በቅድሚያ ይናገሩ፤ በረጅም ዕድሜ ያገኙትን ጥበብ ያስተምሩ’ ብዬ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደዚህም አልሁ፥ “የሚናገሩ ዓመታት አይደሉም፥ በዓመታት ብዛት ሰዎች ጥበብን አያውቋትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደዚህም አልሁ፦ ዓመታት በተናገሩ ነበር፥ የዓመታትም ብዛት ጥበብን ባስተማረች ነበር። |
ንጉሡም ሮብዓም፦ “ለዚህ ሕዝብ እንድመልስለት የምትመክሩኝ ነገር ምንድነው?” ብሎ አባቱ ሰሎሞን በሕይወት ሳለ በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ሽማግሌዎች ጋር ተማከረ።
እስከ አሁን በነበረው ጊዜ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ እንደገና የእግዚአብሔር ቃላት የመጀመሪያውን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ ሰው ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።