ኢዮብ 31:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በትከሻዬ ላይ እሸከመው፥ አክሊልም አድርጌ በራሴ ላይ አስረው ነበር፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርግጥ ትከሻዬ ላይ በደረብሁት፣ እንደ አክሊልም ራሴ ላይ በደፋሁት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ሽልማት ምልክት በደረቴ ላይ አደርጋቸው ነበር። እንደ አክሊልም በራሴ ላይ ባስቀመጥኳቸው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በትከሻዬ ላይ እሸከመው ነበር፥ አክሊልም አድርጌ በራሴ አስረው ነበር፥ በብዙዎችም መካከል አነብበው ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በትከሻዬ ላይ እሸከመው፥ አክሊልም አድርጌ በራሴ አስረው ነበር፥ |
የሚያዳምጠኝ ምነው በኖረልኝ! እነሆ የእጄ ምልክት፥ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ፥ ከባላጋራዬ የተጻፈው የክስ ጽሑፍ ምነው በተገኘልኝ!
የእስራኤል ልጆች የመታሰቢያ ድንጋዮች እንዲሆኑ ሁለቱን ዕንቁዎች በኤፉዱ ትከሻዎች ላይ ታደርጋለህ፤ አሮንም በሁለቱ ትከሻዎቹ ላይ ለመታሰቢያ እንዲሆን ስማቸውን በጌታ ፊት ይሸከማል።