ኢዮብ 31:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ወርቅን ተስፋ አድርጌ፥ ንጹሑንም ወርቅም መተማመኛዬ ብዬ ጠርቼው እንደሆነ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወርቅን ተስፋ አድርጌ፣ ወይም ንጹሑን ወርቅ፣ ‘አንተ መታመኛዬ ነህ’ ብዬ ከሆነ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እምነቴን በሀብት ላይ አድርጌ አላውቅም፤ ወይም ንጹሕ ወርቅንም መታመኛዬ አላደረግሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ወርቄን በመሬት ውስጥ ቀብሬ እንደ ሆነ፥ ዋጋው ብዙ በሆነ ዕንቍ ታምኜም እንደ ሆነ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወርቅን ተስፋ አድርጌ፥ ጥሩውንም ወርቅ፦ በአንተ እታመናለሁ ብዬ እንደ ሆነ፥ |
እንግዲህ በእናንተ ያሉትን ምድራዊ ነገሮች ሁሉ ግደሉ፤ እነርሱም፦ “ዝሙትና ርኩሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣዖትንም ማምለክ የሆነ ስግብግብነት” ናቸው፤
ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፤ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከእምነት ፈቀቅ በማለት መንገዳቸውን ስተው ሄደዋል፥ በብዙም ሥቃይ ራሳቸውን ወግተዋል።
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ በሚያልፍም ባለጠግነት ላይ ሳይሆን እንድንደሰትበት ሁሉን አትረፍርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንዲያደርጉ እዘዛቸው።