ትከሻዬ ከመሠረትዋ ትውደቅ፥ ክንዴም ከመገናኛዋ ትሰበር።
ትከሻዬ ከመጋጠሚያው ይነቀል፤ ክንዴም ከመታጠፊያው ይሰበር፤
ይህን ሁሉ ሳላደርግ ቀርቼ ከሆነ ክንዴ ከትከሻዬ ይውለቅ፤ ከመገናኛውም ተሰብሮ ይለይ፥
ትከሻዬ ከመሠረቷ ትውደቅ፥ ክንዴም ከመገናኛዋ ትሰበር።
ሚስቴ ለሌላ ሰው ትፍጭ፥ ሌሎችም በእርሷ ላይ ይጐንበሱ።
የእግዚአብሔር መዓት አስደንግጦኛልና፥ በክብሩም ፊት ምንም ለማድረግ አልቻልሁም።”
በስንዴ ፋንታ አሜከላ፥ በገብስም ፋንታ ኩርንችት ይውጣብኝ።” የኢዮብ ቃል ተፈጸመ።
ከበደለኞች ብርሃናቸው ተከልክሎአል፥ ከፍ ያለውም ክንድ ተሰብሮአል።
ባላስታውስሽ፥ ምላሴ በጉሮሮዬ ይጣበቅ፥ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ።