ኢዮብ 30:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ አንተ ጮኽሁ፥ አልመለስህልኝም፥ ተነሣሁ፥ ነገር ግን ዝም ብለህ ተመለከትኸኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አምላክ ሆይ፤ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ነገር ግን አልመለስህልኝም፤ በፊትህም ቆምሁ፤ አንተ ግን ዝም አልኸኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ሆይ! አንተን ለመንኩ፤ ነገር ግን አልመለስክልኝም፤ ቆሜም ወደ አንተ ጸለይኩ፤ አንተ ግን ፊትህን አልመለስክልኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ አንተ ጮኽሁ፥ አልሰማኸኝምም፤ እነርሱ ግን ቆመው ተመለከቱኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ አንተ ጮኽሁ፥ አልመለስህልኝም፥ ተነሣሁ፥ አልተመለከትኸኝም። |
የሚያዳምጠኝ ምነው በኖረልኝ! እነሆ የእጄ ምልክት፥ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ፥ ከባላጋራዬ የተጻፈው የክስ ጽሑፍ ምነው በተገኘልኝ!