መንገዱ ለተሰወረበት ሰው፥ እግዚአብሔርም በአጥር ላጠረው ብርሃን ስለምን ተሰጠ?
መንገዱ ለተሰወረበት ሰው፤ እግዚአብሔርም በዐጥር ላጠረው፣ ሕይወት ለምን ተሰጠ?
መንገዱ ለተሰወረበትና እግዚአብሔር ለዘጋበት ሰው ብርሃን የሚሰጠው ለምንድን ነው?
ሞት ለሰው ዕረፍቱ ነው፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ከለከለው።
መንገዱ ለተሰወረበት ሰው፥ እግዚአብሔርም በአጥር ላጠረው ብርሃን ስለ ምን ተሰጠ?
እነሆ፥ ካፈረሰ፥ የፈረሰው ተመልሶ አይሠራም፥ በሰውም ላይ ከዘጋ፥ ሊከፈት አይችልም።
እግሬንም በእግር ግንድ አግብተሃል፥ መንገዴንም ሁሉ ተቆጣጥረሃል፥ የእግሬንም ዱካ ወስነሃል።
ሠራዊቱ አብረው መጡ፥ መንገዳቸውንም በላዬ አዘጋጁ፥ በድንኳኔም ዙሪያ ሰፈሩ።”
እንግዲህ እግዚአብሔር ጥፋተኛ እንዳደረገኝ፥ በመረቡም እንደ ከበበኝ እወቁ።
እንዳላልፍ መንገዴን ዘግቶታል፥ በጎዳናዬም ጨለማ አኑሮበታል።
መቃብርን ባገኙ ጊዜ በእልልታ ደስ ለሚላቸው፥ ሐሤትንም ለሚያደርጉ ሕይወት ስለምን ተሰጠ?
መከራዬን አይተሃልና፥ ነፍሴንም ከጭንቀት አድነሃታልና በምሕረትህ ደስ ይለኛል ሐሤትም አደርጋለሁ።
በእኔ ላይ ቁጣህ ጸና፥ ማዕበልህንም ሁሉ በእኔ ላይ አመጣህ።
የሚያውቁኝን ከእኔ አራቅህ፥ በእነርሱ ዘንድ አጸያፊ አደረግኸኝ፥ ተዘግቶብኛል፥ መውጫም የለኝም።
ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤል ሆይ፦ “መንገዴ ከጌታ ተሰውራለች፥ ፍርዴም በአምላኬ ቸል ተብላለች” ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?
ጋሜል። እንዳልወጣ በዙሪያዬ ቅጥር ሠራብኝ፥ ሰንሰለቴን አከበደ።
መንገዴን በተጠረበ ድንጋይ ዘጋ፥ ጐዳናዬንም አጣመመ።
እንዲሁም የአመንዝራ ልጆች ናቸውና ለልጆችዋ አልራራም።