La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 29:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ከተማይቱ በር በወጣሁ ጊዜ፥ በአደባባዩም ወንበሬን ባኖርሁ ጊዜ፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ወደ ከተማዪቱ በር ብቅ ባልሁ ጊዜ፣ በአደባባይዋም በወንበር በተቀመጥሁ ጊዜ፣

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወደ ከተማም አደባባይ እየሄድኩ በሸንጎ እቀመጥ በነበረ ጊዜ፥

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ገሥ​ግሼ በወ​ጣሁ ጊዜ፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ወን​በ​ሬን ባኖ​ሩ​ልኝ ጊዜ፥

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ከተማይቱ በር በወጣሁ ጊዜ፥ በአደባባዩም ወንበሬን ባኖርሁ ጊዜ፥

Ver Capítulo



ኢዮብ 29:7
12 Referencias Cruzadas  

ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፥ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ። ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፥ አላቸውም፦


ኤሞርና ሴኬም ልጁም ወደ ከተማቸው አደባባይ ገቡ፥ ለከተማቸውም ሰዎች እንዲህ ብለው ነገሩ፦


ወጣቶች እኔን አይተው ይሸሸጉ፥ ሽማግሌዎችም ተነሥተው ይቆሙ ነበር።


በይፋ ድጋፍ አለኝ ብዬ፥ በወላጅ አልባ ላይ እጄን አንሥቼ የቃታሁ እንደሆነ፥


ባሏ በአገር ሽማግሌዎች መካከል በሸንጎ በተቀመጠ ጊዜ በበር የታወቀ ይሆናል።


በበሮች አጠገብ በከተማይቱም መግቢያ፥ በደጆች መግቢያ ትጮኻለች፦


በንጉሡም ቤት የነበረው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ አቤሜሌክ ኤርምያስን በጉድጓዱ ውስጥ እንዳኖሩት ሰማ። ንጉሡም በብንያም በር ተቀምጦ ነበር።


እንግዲህ የምትሠሩት ነገር ይህ ነው፦ እርስ በእርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ፤ በአደባባያችሁም መግቢያዎች ሐቀኛና ትክክለኛ ፍርድ ፍረዱ።


“አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለየነገዶችህ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤ እነርሱም ሕዝቡን በቅን ፍርድ ይዳኙ።


አባትና እናቱ ይዘው በሚኖሩበት ከተማ በር ወዳሉት አለቆች ያምጡት፤


በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሽማግሌዎችና ሌሎችም ሰዎች ሁሉ፦ “እኛ ምስክሮች ነን፥ ጌታ ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ፥ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፥ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተልሔም ይጠራ።