ብርቱ እንደ ነበርኩበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ድንኳኔን ይጠብቅ በነበረበት ጊዜ፥
እኔም ብርቱ ነበርሁ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅነት ቤቴን ይባርክ ነበር፤
ምነው የእግዚአብሔር ረድኤት ቤቴን ይጠብቅ እንደ ነበረበት እንደ ወጣትነቴ ጊዜ በሆንኩ!
በበረከት ሁሉ በነበርሁ ጊዜ፥ እግዚአብሔርም ቤቴን በጐበኘ ጊዜ፥
በሙሉ ሰውነቴ እንደ ነበርሁ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ድንኳኔን በጋረደ ጊዜ፥
እርሱንና ቤቱን በዙሪያውም ያሉትን ሁሉ አላጠርህለትምን? የእጁን ሥራ ባርከህለታል፥ ንብረቱም በምድር ላይ በዝቶአል።
የእግዚአብሔርንስ ምሥጢር ሰምተሃልን? ጥበብን የግልህ ለማድረግ ትመኛለህን?
ሁሉን የሚችል አምላክ ከእኔ ጋር ገና ሳለ፥ ልጆቼም በዙሪያዬ ሳሉ፥
ጌታ ለሚፈሩት ወዳጃቸው ነው፥ ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል።
በመከራ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሸሽጎኛልና፥ በዓለት ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።
በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።
ጠማማ ሁሉ በጌታ ፊት ርኩስ ነውና፥ ወዳጅነቱ ግን ከቅኖች ጋር ነው።
ሞታችኋልና፤ ሕይወታችሁም ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ውስጥ ተሰውሮአልና፤