ኢዮብ 29:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከቃሌ በኋላ አንዳች አልመለሱም፥ ንግግሬም በእነርሱ ላይ ተንጠባጠበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ከተናገርሁ በኋላ፣ የሚናገር ሰው አልነበረም፤ ቃሌም እየተንጠባጠበ በጆሯቸው ይገባ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንግግሬ ያረካቸው ስለ ነበር፥ ከእኔ ንግግር በኋላ የሚናገር ሰው አልነበረም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነገሬ ላይ ደግመው አይናገሩም፤ ባነጋገርኋቸውም ጊዜ ደስ ይላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከቃሌ በኋላ አንዳች አልመለሱም፥ ንግግሬም በእነርሱ ላይ ተንጠባጠበ። |
የያዕቆብ ትሩፍ በብዙ ሕዝቦች መካከል ከጌታ ዘንድ እንደሚመጣ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውን እንደማይጠብቅ፥ የሰውን ልጆች በመጠበቅ እንደማይዘገይ ይሆናል።
ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይዝነብ፤ ንግግሬ እንደ ጠል ይንጠባጠብ፤ በልምላሜ ላይ እንደ ጤዛ፥ በሣርም ላይ እንደ ካፊያ፥ በቡቃያም ላይ እንደሚወርድ ዝናብ፥