ኢዮብ 28:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ዛጐልና ስለ አልማዝ አይነገርም። የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቁ ይልቅ ይበልጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛጐልና አልማዝ ከቍጥር አይገቡም፤ የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍም ይበልጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከበሩ ዛጐልና አልማዝ ከጥበብ ጋር አይወዳደሩም። የጥበብ ዋጋ ከሉልም በላይ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛጎልና አልማዝ አይታሰቡም። አንተ ግን እጅግ ከከበሩ ነገሮች ሁሉ ይልቅ ጥበብን አቅርባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ዛጐልና ስለ አልማዝ አይነገርም። የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍ ይልቅ ይበልጣል። |
ከምርትሽ ብዛት የተነሣ አራም ነጋዴሽ ነበረች፤ ዕቃዎችሽን በበሉር፥ በወይን ጠጅ፥ በወርቀ ዘቦ፥ በጥሩ በፍታም በዛጐልም በቀይ ዕንቁም ይቀይሩ ነበር።
እንዲሁም ደግሞ ሴቶች ከትሕትናና ራስን ከመግዛት ጋር በሚገባ ልብስ ራሳቸውን ያስጊጡ፤ ይሁንና በቄንጠኛ የጸጉር አሠራር ወይም በወርቅ ወይም በዕንቁ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሁን።
ሴቲቱም ሐምራዊና ቀይ ልብስ ለብሳ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፤ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገርና የዝሙትዋ ርኩሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ይዛ ነበር
ጭነቱም ወርቅና ብር፥ የከበረም ድንጋይ ዕንቁም፥ ቀጭንም ተልባ እግር፥ ቀይም ሐር፥ ሐምራዊም ልብስ፥ መልካም መዐዛ ያለውም እንጨት ሁሉ፥ ከዝሆን ጥርስም የተሠራ ዕቃ ሁሉ፥ እጅግም ከከበረ እንጨት፥ ከነሐስም ከብረትም ከዕብነ በረድም የተሠራ ዕቃ ሁሉ፥
ዐሥራ ሁለቱም ደጆች ዐሥራ ሁለት ዕንቁዎች ነበሩ፤ እያንዳንዱም ደጅ ከአንድ ዕንቁ የተሠራ ነበረ። የከተማይቱም መንገድ እንደ መስታወት ብርሃን ከሚያስተላልፍ ከንጹሕ ወርቅ የተሠራ ነበረ።