ኢዮብ 27:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ሁላችሁም አይታችኋል፥ ታዲያ ለምን በከንቱ ትባክናላችሁ?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁላችሁ ይህን አይታችኋል፤ ታዲያ፣ ይህ ከንቱ ንግግር ምንድን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተም እኮ ይህን ሁሉ ታውቃላችሁ፤ ታዲያ ይህን ከንቱ ነገር ለምን ትናገራላችሁ?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ሁላችሁም፥ በክፉዎች ላይ ክፋት እንደምትመጣባቸው ታውቃላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ሁላችሁ አይታችኋል፥ ስለ ምን ከንቱ ሆናችሁ? |
በምድር የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፥ በክፉዎች ላይ የሚደረገው የሚደርስባቸው ጻድቃን አሉ፥ ለጻድቃንም የሚደረገው የሚደርስላቸው ክፉዎችም አሉ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ።