የነቢያት ጉባኤ አባል የነበረ ባሏ የሞተባት አንዲት ሴት ወደ ኤልሳዕ መጥታ “ጌታዬ ሆይ! ባሌ ሞቶብኛል! እርሱም አንተ እንደምታውቀው እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበር፤ ነገር ግን እነሆ ለባሌ ገንዘብ አበድሮት የነበረ አንድ ሰው በባሌ ዕዳ ፈንታ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ወስዶ ባርያ አድርጎ ሊገዛቸው ፈልጎአል” አለችው።
ኢዮብ 24:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቱ የሞተበትን ልጅ ከጡቱ የሚነጥሉ አሉ፥ ከችግረኛውም መያዣ ይወስዳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባት የሌለው ልጅ ከዕቅፍ ተነጥቋል፤ የድኻውም ልጅ በዕዳ ተይዟል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አባቱ የሞተበት ልጅ አገልጋይ እንዲሆናቸው የእናቱን ጡት አስጥለው ይነጥቃሉ፤ የችግረኛውንም ልጅ የዕዳ መያዣ አድርገው ይወስዳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድሃአደጉን ልጅ ከጡቱ ይነጥላሉ፤ ችግረኛውንም ያሠቃያሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድሀ አደጉን ልጅ ከጡቱ የሚነጥሉ አሉ፥ ከችግረኛውም መያዣ ይወስዳሉ። |
የነቢያት ጉባኤ አባል የነበረ ባሏ የሞተባት አንዲት ሴት ወደ ኤልሳዕ መጥታ “ጌታዬ ሆይ! ባሌ ሞቶብኛል! እርሱም አንተ እንደምታውቀው እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበር፤ ነገር ግን እነሆ ለባሌ ገንዘብ አበድሮት የነበረ አንድ ሰው በባሌ ዕዳ ፈንታ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ወስዶ ባርያ አድርጎ ሊገዛቸው ፈልጎአል” አለችው።
አሁንም ሥጋችን እንደ ወንድሞቻችን ሥጋ፥ ልጆቻችንም እንደ ልጆቻቸው ናቸው፤ እነሆ ወንዶች ልጆቻችንና ሴቶች ልጆቻችን ባርያዎች እንዲሆኑ ለማምጣት ተገደናል፥ አንደንድ ሴቶች ልጆቻችን አሁንም ለባርነት ተወስደዋል፤ እርሻችንና የወይን ቦታችን ለሌሎች ስለሆነ ኃይል በእጃችን የለም።”
ጌታ ከአለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋር እንዲህ ሲል ይፋረዳል፤ “የወይኔን ቦታ ያጠፋችሁ እናንተ ናችሁ፤ ከድኾች የዘረፋችሁትም በቤታችሁ ይገኛል፤
“አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ አንዱን ፈንግሎ በመውሰድ ባርያ ሲያደርገው ወይም ሲሸጠው ቢገኝ፥ ፈንጋዩ ይሙት። በዚህ ዓይነት ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።