Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 24:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “አባቱ የሞተበት ልጅ አገልጋይ እንዲሆናቸው የእናቱን ጡት አስጥለው ይነጥቃሉ፤ የችግረኛውንም ልጅ የዕዳ መያዣ አድርገው ይወስዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 አባት የሌለው ልጅ ከዕቅፍ ተነጥቋል፤ የድኻውም ልጅ በዕዳ ተይዟል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አባቱ የሞተበትን ልጅ ከጡቱ የሚነጥሉ አሉ፥ ከችግረኛውም መያዣ ይወስዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ድሃ​አ​ደ​ጉን ልጅ ከጡቱ ይነ​ጥ​ላሉ፤ ችግ​ረ​ኛ​ው​ንም ያሠ​ቃ​ያሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ድሀ አደጉን ልጅ ከጡቱ የሚነጥሉ አሉ፥ ከችግረኛውም መያዣ ይወስዳሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 24:9
9 Referencias Cruzadas  

የነቢያት ጉባኤ አባል የነበረ ባልዋ የሞተባት አንዲት ሴት ወደ ኤልሳዕ መጥታ “ጌታዬ ሆይ! ባሌ ሞቶብኛል! እርሱም አንተ እንደምታውቀው እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበር፤ ነገር ግን እነሆ ለባሌ ገንዘብ አበድሮት የነበረ አንድ ሰው በባሌ ዕዳ ፈንታ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ወስዶ ባሪያ አድርጎ ሊገዛቸው ፈልጎአል” አለችው።


ከአይሁድ ወገኖቻችን ጋር ዘራችን አንድ ነው፤ የእኛ ልጆች ከእነርሱ ልጆች የሚለዩበት ምንም ነገር የለም፤ ይሁን እንጂ የገዛ ልጆቻችንን ለባርነት አሳልፈን ለመስጠት ተገደናል፤ እንዲያውም ከሴቶች ልጆቻችን አንዳንዶቹ ባሪያዎች ሆነዋል፤ ነገር ግን እርሻችንና የወይን ተክል ቦታችን ስለ ተወሰዱ ኀይል የሌለን ሆነናል” በማለት አቤቱታ አሰሙ።


ወንድሞችህን ያለ አንዳች ምክንያት በዋስትና አስይዘሃቸዋል፤ ሌሎችንም ልብሳቸውን ገፈህ ራቊታቸውን አስቀርተሃቸዋል።


ድኾች ምንም ልብስ ሳይኖራቸው ራቁታቸውን ወደ ሥራ ይሰማራሉ። በመከር ወራት ነዶ ተሸክመው እያጋዙ እነርሱ ይራባሉ።


በተራራ ላይ በሚዘንበው ዝናብ ሰውነታቸው ይረሰርሳል፤ መጠለያም አጥተው ቋጥኝ ተጠግተው ያድራሉ።


ይህም የሆነው የድኾችን ጩኸት ሰምቼ እታደጋቸውና፥ ወላጆቻቸው የሞቱባቸውንም ልጆች እረዳቸው ስለ ነበረ ነው።


በሙት ልጅ ላይ ዕጣ ትጣጣላላችሁ፤ ወዳጆቻችሁን ለመሸጥ የዋጋ ክርክር ታደርጋላችሁ!


ስለዚህ የሕዝቡን መሪዎችና አማካሪዎች ወደ ፍርድ አቅርቦ እንዲህ ይላቸዋል፦ “የወይኑን አትክልት ቦታ ዘረፋችሁ፤ ከድኾች በተዘረፈው ሀብትም ቤታችሁን ሞላችሁ።


“እስራኤላዊ ወገኑን አፍኖ በመውሰድ ባሪያ አድርጎ የሚጠቀምበትና ወይም ለሌላ ሰው በባርነት አሳልፎ የሚሸጠው ማንም ሰው በሞት ይቀጣ፤ በዚህም ዐይነት ክፉ ነገርን ታስወግዳላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos