La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 24:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በእነዚህ ሰዎች አጥር ውስጥ ዘይት ያወጣሉ፥ ወይንም ይጠምቃሉ፥ ነገር ግን ይጠማሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በየተረተሩ የወይራ ዘይት ያወጣሉ፤ ወይን እየጠመቁ፣ ራሳቸው ግን ይጠማሉ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በክፉ ሰዎች የአትክልት ቦታ ከወይራ ፍሬ ዘይት ያወጣሉ፤ ከወይን ዘለላም የወይን ጠጅን ይጠምቃሉ፤ እነርሱ ግን ይጠማሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በጠ​ባብ ቦታ በዐ​መፅ ይሸ​ም​ቃሉ፥ የጽ​ድ​ቅ​ንም መን​ገድ አያ​ው​ቁም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በእነዚህ ሰዎች አጥር ውስጥ ዘይት ያደርጋሉ፥ ወይንም ይጠምቃሉ፥ ነገር ግን ይጠማሉ።

Ver Capítulo



ኢዮብ 24:11
7 Referencias Cruzadas  

ያለ ልብስ ራቁታቸውን ይሄዳሉ፥ ተርበው ነዶዎችን ይሸከማሉ፥


በከተማው ለመሞት የሚያጣጥሩ ያቃስታሉ፥ ቁስለኞችም ለእርዳታ ይጮኻሉ፥ እግዚአብሔር ግን ልመናቸውን አይመለከትም።”


“እነርሱ በውኃ ላይ ተንሳፈው ያልፋሉ፥ ድርሻቸውም በምድር ላይ የተረገመች ናት፥ ወደ ወይኑ ቦታ መንገድ አይመለሱም።


ደስታና ሐሴትም ከፍሬያማው እርሻ ተወስዶአል፤ በወይኑም ቦታዎች ዝማሬና እልልታ የለም፤ በመጥመቂያም ወይን የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮቹን እልልታ አጥፍቻለሁ።


“ቤቱን በግፍ ሰገነቱንም በዓመፅ ለሚሠራ፥ ባልንጀራውንም እንዲያው በከንቱ ለሚያሠራ፥ ዋጋውንም ለማይሰጠው፤


“እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር።


እነሆ፥ እርሻችሁን ሲያጭዱ ለዋሉ ሠራተኞች ያልከፈላችሁት ደመወዝ በእናንተ ላይ ይጮኻል፤ የአጫጆቹም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ጆሮ ደርሶአል።