ኢዮብ 23:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ በፊቱ ደነገጥሁ፥ ባሰብሁም መጠን ፈራሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፊቱ የደነገጥሁትም ለዚህ ነው፤ ይህን ሁሉ ሳስብ እፈራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በእርሱ ፊት መቆም እጅግ ያስፈራኛል፤ ይህን ባሰብኩ ጊዜ እንኳ ፈራሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ በፊቱ ደነገጥሁ፤ አስበዋለሁ፤ ከእርሱም የተነሣ እፈራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በፊቱ ደነገጥሁ፥ ባሰብሁም ጊዜ ከእርሱ ፈራሁ። |
እኔ ሰምቻለሁ፥ አንጀቴ ራደብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መበስበስ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በውስጤም ተንቀጠቀጥሁ፥ በአስጨነቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፥ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።