ኢዮብ 22:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃይለኛ ሰው መሬት ገዛ፥ የተከበረ ሰው ተቀመጠባት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባለርስትና ኀያል፣ በርሱም የምትኖር ክቡር ሰው ብትሆንም፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድር የኀይለኛ ሰዎች ንብረት፥ የተወሰኑ ሰዎች ብቻ ይዞታ ሆናለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፊታቸውን አይተህ ያደነቅሃቸው አሉ፥ በምድርም ላይ ድሆችን በዐመፅ ጠላህ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በክንድ የበረታ ምድርን ገዛ፥ ከበርቴውም ሰው ተቀመጠባት። |
እጆቻቸው ክፉ ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ልዑሉና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጉናሉ።