ኢዮብ 22:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዳያይ የጠቈረ ደመና ጋርዶታል፥ በሰማይ ክበብ ላይ ይራመዳል” ብለሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰማይ ክበብ ላይ ሲራመድ፣ እንዳያየን ጥቅጥቅ ያለ ደመና ይሸፍነዋል።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠፈር ላይ ሲመላለስ ድቅድቅ ደመና ስለሚጋርደው ሊያይ አይችልም’ ትላለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠቈረ ደመና ጋርዶታል አያይምም፤ በሰማይ ክበብ ላይ ይራመዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዳያይ የጠቈረ ደመና ጋርዶታል፥ በሰማይ ክበብ ላይ ይራመዳል ብለሃል። |
እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፥ በእርሷም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥
አዳራሹን በሰማይ የሠራ፥ ጠፈሩንም በምድር ላይ የመሠረተ፥ የባሕርንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሰው እርሱ ነው፤ ስሙም ጌታ ነው።