ኢዮብ 22:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እግዚአብሔር በላይ በሰማያት አይደለምን? ከዋክብትም እንዴት ከፍ ባለ ስፍራ ላይ እንዳሉ ተመልከት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር ከፍ ባለው ሰማይ የሚኖር አይደለምን? በሩቅ ከፍታ ያሉትን ከዋክብት ያያል! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ከፍ ባለው ሰማይ የሚኖር አይደለምን? ከዋክብት ምንም እንኳ ከፍ ባለ ስፍራ ቢሆኑ፥ እርሱ ከበላያቸው ሆኖ ይመለከታቸዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ልዑል የወደደውን ያደርግ ዘንድ የሚገባው አይደለምን? ትዕቢተኞችንስ አያዋርዳቸውምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በሰማያት ከፍ ከፍ አይልምን? ከዋክብትም እንዴት ከፍ ከፍ እንዳሉ ተመልከት። |
እግዚአብሔር በሰማይ፥ አንተም በምድር ነህና በአፍህ አትቸኩል፥ ልብህም በእግዚአብሔር ፊት ቃልን ለመናገር አይቸኩል፥ ስለዚህም ቃልህ ጥቂት ትሁን።
ለዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።