ኢዮብ 21:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ባሰብሁ ቍጥር እደነግጣለሁ፥ ሰውነቴንም መንቀጥቀጥ ይይዘዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ነገር ባሰብሁ ቍጥር እደነግጣለሁ፤ ሰውነቴም በፍርሀት ይንቀጠቀጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እንኳ ሳስበው ያስደነግጠኛል፤ ሰውነቴንም በፍርሃት ያንቀጠቅጠዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ባሰብሁ ቍጥር እጨነቃለሁ፤ ጻዕርም ሥጋዬን ይይዛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ባሰብሁ ቍጥር እጨነቃለሁ፥ ፃዕርም ሥጋዬን ይይዛል። |
እኔ ሰምቻለሁ፥ አንጀቴ ራደብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መበስበስ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በውስጤም ተንቀጠቀጥሁ፥ በአስጨነቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፥ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።