ኢዮብ 21:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ መንገዱ ፊቱ ለፊት የሚወቅሰው ማን ነው? ስለ ሠራውስ የሚቀጣው ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተግባሩን ፊት ለፊት የሚነግረው ማን ነው? የእጁንስ ማን ይሰጠዋል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉውን ሰው ስለ መጥፎ ጠባዩ የሚወቅሰው ማን ነው? በክፉ ሥራውስ የሚቀጣው ማን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንገዱን በፊቱ የሚናገር ማን ነው? እርሱ የሠራውንስ የሚመልስበት ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገዱን በፊቱ የሚናገር ማን ነው? የሠራውንስ የሚመልስበት ማን ነው? |
እርሱም ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ኩነኔ ሲነጋገር ሳለ፥ ፊልክስ ፈርቶ “አሁንስ ሂድ፥ በተመቸኝም ጊዜ ልኬ አስጠራሃለሁ፤” ብሎ መለሰለት።
“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ፤ ይላል ጌታ” ተብሎ ተጽፎአልና፥ ተወዳጆች ሆይ! ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ለቁጣው ቦታ ስጡ እንጂ።