ኮርማቸው ይወልዳል፥ ዘሩንም አይጥለውም፥ ላማቸውም ትወልዳለች፥ አትጨነግፍም።
ኰርማቸው ዘሩ በከንቱ አይወድቅም፤ ያስረግዛል፤ ላማቸውም ሳትጨነግፍ ትወልዳለች።
ከብቶቻቸው ያለአንዳች ችግር ይረባሉ፤ ላሞቻቸውም ምንም ሳይጨነግፉ ይወልዳሉ።
በሬዎቻቸው አይመክኑም፤ ላሞቻቸውም አይጨነግፉም፤ በደኅናም ይወልዳሉ።
ሕፃኖቻቸውን እንደ መንጋ ይለቃሉ፥ ልጆቻቸውም ይቧርቃሉ።
ቤታቸው በሰላም ከፍርሃት ነጻ ነው፥ የእግዚአብሔርም በትር የለባቸውም።
በምድርህ የምትጨነግፍ ወይም መካን አትኖርም፤ የዘመንህን ቍጥር እሞላለሁ።
“በሐምራዊና በክት ልብስ የሚሽቀረቀር አንድ ሀብታም ሰው ነበረ፤ ዕለት ዕለትም እየተመቸው በቅንጦት ይኖር ነበር።
ጌታ ሊሰጥህ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር በሆድህ ፍሬ፥ በከብትህ ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ፥ ብልጽግና ይሰጥሃል።