Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 28:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጌታ ሊሰጥህ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር በሆድህ ፍሬ፥ በከብትህ ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ፥ ብልጽግና ይሰጥሃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እግዚአብሔርም ሊሰጥህ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር በማሕፀንህ ፍሬ፣ በእንስሳትህም ግልገል፣ በምድርህም ሰብል የተትረፈረፈ ብልጽግና ይሰጥሃል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔር ለአንተ ይሰጥህ ዘንድ ለቀድሞ አባቶችህ በማለላቸው ምድር ብዙ ልጆችን፥ ብዙ የቀንድ ከብትና የተትረፈረፈ የእርሻን ሰብል ይሰጥሃል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እር​ስ​ዋን ይሰ​ጥህ ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ችህ በማ​ለ​ላ​ቸው በም​ድ​ርህ ላይ፥ በሆ​ድህ ፍሬ፥ በእ​ር​ሻ​ህም ፍሬ፥ ከብ​ቶ​ች​ህን በማ​ብ​ዛት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ​ነ​ቱን ያበ​ዛ​ል​ሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እግዚአብሔርም እርስዋን ይሰጥህ ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው በምድርህ ላይ፥ በሆድህ ፍሬ፥ በከብትህ ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ፥ እግዚአብሔር በጎነቱን በላይህ ያበዛል።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 28:11
10 Referencias Cruzadas  

ጌታ በአባቶችህ ደስ እንዳለው በመልካሙ ነገር ሁሉ እንደገና በአንተ ደስ ይለዋልና፥ ጌታ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ፥ በሆድህም ፍሬ፥ እንዲሁም በከብትህም ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ እጅግ ያበለጽግሃል።


የጌታ በረከት ሀብታም ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ከእርሷ ጋር አይጨምርም።


“የማሕፀንህ ፍሬ፥ የምድርህ አዝመራ፥ የእንስሳትህ ግልገሎች፥ የከብትህ ጥጃ፥ የበግና የፍየል ግልገሎችህም ይባረካሉ።


ወደ እናንተም ዘወር ብዬ በበጎ እመለከታችኋለሁ፥ እንድታፈሩም አደርጋችኋለሁ፥ አበዛችሁማለሁ፤ ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ።


ጌታ ለዳዊት በእውነት ማለ አይጸጸትምም፥ እንዲህ ብሎ፦ ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።


ሚስቴ እስትንፋሴን ጠላች፥ የእናቴም ማኅፀን ልጆች ተጸየፉኝ።


እነሆ፥ ምድሪቱን በፊታችሁ አኖራለሁ፥ ግቡ፥ ጌታ ለእነርሱ ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ይሰጣት ዘንድ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውንም ምድር ውረሱ።’


ይወድድህማል፥ ይባርክህማል፥ ያበዛህማል፤ ይሰጥህም ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር የሆድህን ፍሬ እንዲሁም የምድርህንም ፍሬ፥ እህልና ወይንህን፥ ዘይትህንም፥ በከብትም ብዛት በበግም መንጋ አብዝቶ ይባርክልሃል።


ባረካቸውም እጅግም በዙ፥ እንስሶቻቸውንም አላሳነሰባቸውም።


እነሆ፥ ልጆች የጌታ ስጦታ ናቸው፥ የማሕጸንም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios