ኢዮብ 2:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊትም ከእርሱ ጋር በምድር ላይ ተቀመጡ፥ ሕመሙም እጅግ እንደ በዛ አይተው ነበርና ከእነርሱ አንድ ቃል የሚናገረው አልነበረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊት ከርሱ ጋራ መሬት ላይ ተቀመጡ፤ ሥቃዩ ታላቅ መሆኑንም ስለ ተረዱ፣ አንዳች ቃል የተናገረው አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሥቃዩንም ብዛት ስላዩ ምንም ቃል ሳይናገሩ ከእርሱ ጋር ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊት በመሬት ላይ ተቀምጠው ሰነበቱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊትም በአጠገቡ ተቀመጡ፤ ሕማሙ እጅግ አስፈሪና ታላቅ እንደ ነበረ አይተዋልና ከእነርሱ አንድ ቃል የሚናገረው አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊትም ከእርሱ ጋር በምድር ላይ ተቀመጡ፥ ሕመሙም እጅግ እንደ በዛ አይተዋልና ከእነርሱ አንድ ቃል የሚናገረው አልነበረም። |
አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ ከዚህ በኋላ ቅንጡና ቅምጥል አትባይምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ።
ዮድ። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፥ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፥ ማቅም ታጠቁ፥ የኢየሩሳሌም ደናግል ራሳቸውን ወደ ምድር አዘነበሉ።