ኢዮብ 19:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍርድ እንዳለ ታውቁ ዘንድ ቁጣ የሰይፍን ቅጣት ያመጣልና ከሰይፍ ፍሩ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቍጣ በሰይፍ መቀጣትን ያስከትላልና፣ ራሳችሁ ሰይፍን ፍሩ፤ በዚያ ጊዜ ፍርድ እንዳለ ታውቃላችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ቊጣ የሰይፍን ቅጣት ስለሚያስከትል ሰይፍ እንዳይበላችሁ ተጠንቀቁ። የእግዚአብሔር ፍርድ መኖሩንም ዕወቁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ሐሣርን ፍሩአት፥ ቍጣ በኃጥኣን ላይ ይመጣልና፤ ያንጊዜም ክፋታቸው ከየት እንደ ሆነ ያውቃሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍርድ እንዳለ ታውቁ ዘንድ ቍጣ የሰይፍን ቅጣት ያመጣልና ከሰይፍ ፍሩ። |
አንተ ጐበዝ፥ በጉብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጉብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፥ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ እወቅ።