እነሆም፥ ብርቱ ነፋስ ከምድረበዳ መጥቶ የቤቱን አራቱን ማዕዘን መታው፥ በብላቴኖቹም ላይ ወደቀ፥ ሞቱም፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ።”
ኢዮብ 19:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልጋዬን ብጠራ አይመልስልኝም፥ በአፌም መለማመጥ አለብኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋዬን ብጣራ፣ በአንደበቴም ብለምነው፣ አይመልስልኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገልጋዬን ስጠራው መልስ አይሰጠኝም እባክህ እርዳኝ ብዬ ስለምነውም እንኳ እሺ አይለኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አገልጋዮችን እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱ ግን ቸል ይሉኛል፤ በአፌም እለማመጣቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዬን ብጠራ፥ በአፌም ባቈላምጥ አይመልስልኝም። |
እነሆም፥ ብርቱ ነፋስ ከምድረበዳ መጥቶ የቤቱን አራቱን ማዕዘን መታው፥ በብላቴኖቹም ላይ ወደቀ፥ ሞቱም፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ።”