በምድር ላይ የሸምቀቆ ገመድ፥ በመንገዱም ላይ ወጥመድ ለእርሱ ተሰውራለች።
በምድር ላይ የሸንበቆ ገመድ፣ በመንገዱም ላይ ወጥመድ በስውር ይቀመጥለታል።
በመሬት ላይ የሸምቀቆ ገመድ ተዘርግቶለታል፤ በመንገዱም ወጥመድ ተዘጋጅቶአል።
በምድር ላይ የሸምቀቆ ገመዱ ተሰውራለች፤ የሚጐትተውም በመንገዱ ላይ ነው።
ድንጋጤ በዙሪያው ታስፈራዋለች፥ በስተ ኋላውም ሆና ታባርራቸዋለች።
አሽክላ ሰኰናውን ይይዛል፥ ወጥመድም ይበረታበታል።
በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምንና ዲንን ያዘንባል የሚያቃጥል ነፋስም የጽዋቸው እድል ፈንታ ነው።
መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፥ በወጥመዴም ይያዛል፥ ወደ ከለዳውያን ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፥ ሆኖም አያያትም በዚያም ይሞታል።
ዳዊትም፥ ማዕዳቸው ወጥመድና አሽክላ ማሰናከያም ፍዳም ይሁንባቸው፤