La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 16:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወዳጆቼ ናቁኝ፥ ዓይኔም በእግዚአብሔር ፊት እንባ ታፈሳለች።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወዳጆቼ በንቀት ቢመለከቱኝም፣ ዐይኔ ወደ እግዚአብሔር ያነባል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወዳጆቼ በንቀት ይመለከቱኛል፤ እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር አለቅሳለሁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“አሁ​ንም፥ እነሆ፥ ምስ​ክሬ በሰ​ማይ አለ፤ የሚ​ያ​ው​ቅ​ል​ኝም በአ​ር​ያም ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ይድረስ፥ ዓይኔም በፊቱ እንባ ታፍስስ።

Ver Capítulo



ኢዮብ 16:20
15 Referencias Cruzadas  

“እግዚአብሔር ሆይ! በታማኝነትና በቅንነት እንዳገለገልኩህ፥ አንተ የምትደሰትበትንም ነገር ለማድረግ ዘወትር እጥር እንደ ነበር ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ!” እያለ በመጸለይ ምርር ብሎ አለቀሰ።


ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀላ፥ የሞት ጥላ በዐይኖቼ ቆብ ላይ አለ፥


የሰው ልጅ ከባልንጀራው ጋር እንደሚምዋገት፥ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመምዋገት ምነው በቻለ!


እኔ ደግሞ እንደ እናንተ እናገር ዘንድ ይቻለኝ ነበር፥ ነፍሳችሁ በነፍሴ ፋንታ ቢሆን ኖሮ፥ እኔ በእናንተ ላይ ቃል ማሳካት፥ ራሴንም በእናንተ ላይ መነቅነቅ በተቻለኝ ነበር።


አሁን ግን አድክሞኛል፥ ወገኔንም ሁሉ አፍርሰሃል።


አላጋጮች በእኔ ዘንድ አሉ፥ ዓይኔም ማስቈጣታቸውን ትመለከታለች።


ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ፈዘዘች፥ መላ ሰውነቴ እንደ ጥላ ሆነ።


“ወንድሞቼን ከእኔ ዘንድ አራቀ፥ የሚያውቁኝም አጥብቀው ተለዩኝ።


እርሱን እንዴት እንደማገኘው ምነው ባወቅሁ! ወደ ተቀመጠበትስ ስፍራ ምነው በደረስሁ!


በፍቅሬ ፋንታ ከሰሱኝ፥ እኔ ግን እጸልያለሁ።


በሙሉ ድምጼ ወደ ጌታ ጮኽሁ፥ በሙሉ ድምጼ ወደ ጌታ ለመንሁ።


እርሱም ሥጋ ለብሶ በምድር በሚመላለስ ጊዜ፥ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል፥ ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ስለ ጻድቅ ፍርሃቱም ጸሎቱ ተሰማለት፤