እንደ ወይን ያልበሰለውን ዘለላ ያረግፋል፥ እንደ ወይራ አበባውን ይጥላል።
ፍሬው በጮርቃነት እንደ ተለቀመበት የወይን ተክል፣ አበባውም እንደ ረገፈበት የወይራ ዛፍ ይሆናል።
ገና ሳይበስል ዘለላውን እንደሚያረግፍ የወይን ተክልና አበባው እንደሚረግፍ የወይራ ዛፍ ይሆናል።
ጮርቃውም ይረግፋል፤ እንደ ወይራም አበባ ይወድቃል።
እንደ አበባ ይፈካል፥ ይረግፋልም፥ እንደ ጥላም ይሸሻል፥ እርሱም አይጸናም።
ጌታን መፍራት ዘመንን ታረዝማለች፥ የከፉዎች ዕድሜ ግን ታጥራለች።
ምድሪቱ አለቀሰች ከሳችም፤ ሊባኖስ አፈረ ጠወለገም፤ ሳሮን እንደ ምድረ በዳ ሆነ፤ ባሳንና ቀርሜሎስ ቅጠላቸውን አረገፉ።
በለስም በብርቱ ነፋስ ስትናውጥ ያልበሰለ ፍሬ እንደሚረግፍ የሰማይ ከዋክብትም ወደ ምድር ወደቁ፤